በአቶ ሞሃመድ አብዲ ሃሞ ስምና ምስል የተከፈተ የፌስቡክ አካውንት ጉዳይ!
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሱማሌ ክልል የአፍዴር ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ቀደም ባሉት ዓመታት የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊና የክልሉ ምክር ቤት አባል በነበሩት አቶ ሞሃመድ አብዲ ሃሞ ስምና ምስል የተከፈተ ይህ የፌስቡክ አካውንት ሀሠተኛ መሆኑን አቶ ሞሃመድ ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቀዋል።
የፌስቡክ አካውንቱ እርሳቸው ያልተናገሯቸውን፣ የተዛቡና ሀሠተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ መሆኑን የገለጹት አቶ ሞሃመድ፣ የእርሳቸው ትክክለኛ አካውንት በሚከተለው ሊንክ የተያያዘው ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል: https://m.facebook.com/mahamed.abdi.773
ትክክለኛ ገፆችን፣ አካውንቶችን እንዲሁም ቻናሎችን ብቻ በመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል አስተዋፅኦ ያድርጉ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::