መረጃ ስንፈልግ የምንጎበኛቸው ድረ- ገጾች እና የማህበራዊ ትስስር ገጾች የምነገኘው መረጃ ሁሉ እውነት ነው?
በየቀኑ መረጃ ስንፈልግ የምንጎበኛቸው በርከት ያሉ የሚዲያ ድረ- ገጾች እና የማህበራዊ ትስስር ገጾች አሉ። ከሁሉም ድረ-ገጾች እና የማህበራዊ ትስስር ገጾች እውነተኛ መረጃ እናገኛለን ማለት ግን አይደለም። አንዳንዶቹ በአንጻራዊነት እውነተኛና ታማኝ መረጃ ያደርሳሉ።
በአንጻራዊነት እውነተኛና ታማኝ መረጃ የሚያደርሱ ሚዲያዎች በድረ-ገጻቸው እና በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዲሁም በዘገባዎቻቸው የሚከተሉትን ጠቃሚ ማብራሪያዎች እና መረጃዎች በግልጽ ያስቀምጣሉ።
· ስለ ኤዲቶሪያል ነጻነታቸው ያብራራሉ (a statement of editorial independence):- በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች ነጻና ገለልተኛ ስለምሆናቸው ወይንም የሶስተኛ ወገን ተጽዕኖ እንደሌለባቸው ማብራሪያ ይሰጣሉ።
· ስለ ሚዲያው ማንነት በግልጽ ይናገራሉ (an ‘About’ page for the publication):- በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚድያዎች ስለማንነታቸው እና ስለሚሰሩት ስራ ያብራራሉ። አድራሻቸውን (ቦታ፣ ስልክ ቁጥር፣ ኢሜል፤ ወዘተ) በግልጽ ያሳውቃሉ።
· ስለጋዜጠኞቻቸው ማንነት የተሟላ መረጃ ይሰጣሉ (reporters bios and contact information) በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች ስለዘጋቢዎች፣ ስለጸሀፊዎችና አርታኢዎች ዳራ (bio) የሚያብራሩ ሲሆኑ አድራሻቸውንም ያስቀምጣሉ።
· የመረጃቸውን ምንጭ ግልጽ ያደርጋሉ:- በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች የመረጃ ምንጫቸውን ማንነት በግልጽ ያሳውቃሉ።
· የዘጋቢውን ወይንም የጸሀፊውን ስም ይጠቅሳሉ (byline on news and articles):- በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች የዜናውን ዘጋቢ ወይንም የጽሁፉን ጸሃፊ ስም በግልጽ ያስቀምጣሉ።
· ስለ ፎቶግራፎች በቂ መረጃ ይሰጣሉ (Caption and source information for photos):- በአንጻራዊነት እውነተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች ስለተጠቀሟቸው ፎቶግራፎች ማብራሪያ (caption) ይሰጣሉ። እንዲሁም የፎቶግራፍ አንሽውን ማንነት በግልጽ ይናገራሉ ወይንም ምንጩን ይጠቅሳሉ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::