በምርጫ ወቅት የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን ለመዋጋት የሌሎች ሃገሮች ልምዶች ምን ይመስላሉ?
በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት እንደሚስተዋለው ከሆነ በምርጫ ወቅት የተዛቡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭታቸው ይበዛል። የተለያዩ ሀገራት በምርጫ ወቅት ዙሪያ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመዋጋት ከሚያደርጓቸው መዘጋጀቶች ውስጥ:
1. በምርጫ ዙሪያ የተሳሳቱ መረጃዎች እንደሚሰራጩ መጠበቅ እና የመከላከያ መንገዶችን ማዘጋጀት ዋናው እና አስፈላጊው ደረጃ ነው። እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች ከየት እንደሚነሱ ማለትም ከውጪ ጣልቃ ገቦች ወይስ ከውስጥ ነው የሚለውን መጠየቅ አለብን። በ2019 በኢራን ጣልቃገብነት የታየባቸው ወደ 783 የፌስቡክ ገጾች ተወግደዋል። ካናዳም እንዲሁ በየአመቱ በምታደርገው የትዊተውር ፖስቶች አናልይሲስ ከ9.6 ሚሊዮን ትዊቶች ውስጥ ብዙ ትሮሎች አግኝታለች። ከውስጥ ከሚመጡ ጣልቃ ገብነት ወስጥ ደግሞ በምርጫ ዙሪያ ብቻ የተደራጁ በርካታ የትሮል አካውንቶችን እንዳገኙ እነ ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ጀርመን እና የመሳሰሉት ሃገራት አሳውቀዋል።
2. ሌላው እነዚህን የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመዋጋት ሌሎች ሃገራት ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች ውስጥ አንዱ የሃገሪቷን በተለይ ደግሞ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የመንግስት ድርጅቶች የበይነመረብ ደህንነቶቻቸውን (cyber security) መጠበቅ መቻል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ የእስራኤል የብሄራዊ የበይነ-መረብ ደህንነቶት ድርጅት በምርጫ ውቅት ስራውን አጠንክሮ ይሰራል።
3. ሌላው የተሳሳተ መረጃዎችን በህግ በተደነገገ መልኩ ከማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ የማስወገድ ስራ ነው። እንደ አውስትራሊያ እና ኢራን ባሉ ሃገራት የሰዎችን ደህንነት ወይም የብሄራዊ ደህንነትን የሚጎዳ ከሆነ ያንን መረጃ ማስወገድም ሆነ የሚያሰራጭውን ወገን ወደ ህግ ማቅረብ የሚቻልበት ህግ አጽድቀዋል። ከማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎችም በተጨማሪም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ድረ-ገጾችን የመዝጋትም መብት ይህ ህግ ይሰጠዋል።
4. ሌላው ደግሞ እንደ አውስትራሊያ፣ አርጀንቲና፣ ካናዳ የመሳሰሉት ሀገሮች የህዝባቸውን የdigital literacy ለማሳደግ ሲባል የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማስታወቂያዎችን ከማውጣት እስከ የተለያዩ ፅሁፎችን እስከማሳተም ድረስ ህዝባቸውን ለማንቃት ይሰራሉ።
5. እንደ አውሮፓ ህብረት ያሉ አካላት ደግሞ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመሆን በሚዲያዎች ዙሪያ ጥናቶችን ያስጠናሉ። ለምን እንደዚህ ጥግ የያዘ እንደሆነ እና የመሳሰሉትን ጥናቶች አካሂደው ወደ መፍትሄዎች ለመሄድ ይሞክራሉ።
6. እንደ እስራሌል እና ግብጽ ያሉ ሃገሮች ደግሞ ለሃገሪቱ ህዝቦች መረጃን በማጣራት እና መረጃን ለህዝቡ ለማድረስ የራሳቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ለማበረታታት citizen reporting መንገድ ይጠቀማሉ።
7. ሌላው እና አስፈላጊው ደግሞ ሚዲያዎችን ማስተባበር እና ስለ ምርጫ አዘጋገብ ስልጠናዎችን አቅርቦ የተሻለ የሚዲያ ዘገባ እንዲኖር ማስቻል ነው።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::