የሰኞ መልዕክት
ሁላችንም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የየበኩላችንን አስተዎፅዖ ማድረግ እንዳለብን ሁሉ በቫይረሱ ዙሪያ የሚሰራጩ የሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስም መረባረብ አለብን።
የአለም ጤና ድርጅትን የመሳሰሉ ድርጅቶች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚነሱ የመረጃ መዛባቶችን እና የሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከታተል ሲሉ የኮሚኒኬሽን እና የሶሻል ሚዲያ ባለሙያዎችን የያዘ ቡድን በማሰማራት በማህበራዊ ሚድያ ገጾች ላይ የሚታዩትን የመረጃ መዛባቶች እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
እንደ አለም ጤና ድርጅት አባባል ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት ተከትሎ እነዚህ የሀሰት ዜናዎች እና መረጃዎች ማህበረሰቦችን እየጎዱ ይገኛሉ፣ የተሳሳቱ መድሃኒቶች እና ስለቫይረሱ አመጣጥ የሚያስረዱ የሀሰት መረጃዎች የተለያዩ ችግሮችን ሲያስከትሉም አይተናል።
በተለይ ማህበረሰብን ሊጎዱ ይችላሉ በሚባሉ መረጃዎች እና ዜናዎች ላይ የአለም የጤና ድርጅት ማስረጃዎችን መሰረት ያደረጉ ዜናዎችን ሲያስተካክል ተስተውሏል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::