የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ዙሪያ ምን አሉ?

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር የሞከሩ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ!

ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ የሚቃጡ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በማስቀረት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አመልክቷል።

Via FBC

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::