የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አቋረጠ፣ ግማሹን ቀነሰ ወዘተ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ

ኢትዮጵያ ቼክ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ሀላፊ የሆኑትን አምባሳደር ዮሀን ቦርግስታምን በጉዳዩ ዙርያ አነጋግሯል።
አምባሳደሩ እንደሚሉት ህብረቱ ለኢትዮጵያ ከ2014 እስከ 2020 እአአ ላለው ግዜ 1.4 ቢልዮን ዩሮ መድቧል። ከዚህ ውስጥ 500 ሚልዮን ዩሮ ገደማው ለመንግስት በጀት ድጎማ ይውላል ያሉ ሲሆን 90 ሚልዮን ዩሮ ያክሉ የበጀት ድጎማ ግን አሁን ላይ ክፍያው እንዲዘገይ መደረጉን አረጋግጠዋል።
የአውሮፓ ህብረት ለምን 90 ሚልዮን ዩሮ የበጀት ድጎማውን እንዲዘገይ እንዳረገ ሲያስረዱ በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር እንደሚያያዝ ጠቅሰው “ሁሉም አካላት የሲቪሎች ደህንነትን እንዲጠብቁ፣ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆም፣ ስደተኞች ከለላ እንዲደረግላቸው፣ ቦታዎች ለሰብአዊ እርዳታ ክፍት እንዲሆኑ፣ ክልሉ ለሚድያዎች ክፍት እንዲሆን እንዲሁም መንግስት የጀመረው የተቋረጡ መገናኛዎች የመመለስ ስራ እንዲሰራ ህብረቱ ይፈልጋል” ብለዋል።
ህብረቱ ሙሉ ለሙሉ ድጋፉን እንዳቋረጠ እየተነገረ እና እየተፃፈ ያለው ግን ስህተት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::