በባህር ዳር ከተማ ስለ ውሃ መበከል የከተማው የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ምን አለ?

በባሕር ዳር ከተማ ውሃ ተበክሏል በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከዚህ በፊትም የከተማውን ሕዝብ ሰላም ለመንሳት በተደጋጋሚ ውሃ እንደተበከለ ተደርጎ በሀሰት ይወራ እንደነበር የአገልግሎቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በሪሁን አለሙ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ዛሬና ትናንት በተደረገ የናሙና ምርመራ ምንም ችግር እንደሌለ መረጋገረጡንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::